የሚያሸንፈው ፓርቲ አንድነቷ የተጠበቀች ኢትዮጵያን እንዲያስቀጥል ሕዝባዊ ኀላፊነት ይጣልበታል።
አዲስ አበባ: ግንቦት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምርጫ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው። የሕዝብን ሉዓላዊነት በተግባር የሚያሳይ፤ ሥልጣን በሰላማዊ መንገድ የሚሸጋገርበት እና የዜጎች ተሳትፎ የሚረጋገጥበት ሂደትም ነው።
ዜጎች መሪዎቻቸውን በመምረጥ የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው እንዲወስኑ...
“ማንም ይመረጥ ማን የሕዝብ ድምጽ ማክበር ይገባል” የቆቦ ከተማ ነዋሪዎች
ወልድያ፡ ግንቦት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ምርጫ ክልል በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤት ለሕዝብ ይፋ እየተደረገ ይገኛል።
የምርጫ ጣቢያዎችን ጊዜያዊ ውጤት ሲመለከቱ አሚኮ ያገኛቸው የቆቦ ከተማ ነዋሪዎች ምርጫው ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊ እና...
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
ባሕርዳር፡ ግንቦት 25/2018 ዓ.ም(አሚኮ) በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች የተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በከፍተኛ ስኬት፣ ሥልጡን እና ሕዝባዊ ተሳትፎ በጎላበት መልክ በታላቅ የሕዝብ ድል መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ተወዳዳሪ የሌለው ሚና ለተጫወቱት የክልሉ...
ከምርጫ ማግሥት ለሀገር ሰላም እና ልማት መሥራት ይገባል።
ደብረ ታቦር: ግንቦት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የድምጽ ውጤት ይፋ አድርገዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎችም በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ጊዜያዊ የድምፅ ውጤቶችን እየተመለከቱ ነው።
ውጤቱን ሲመለከቱ ካገኘናቸው መካከል አቶ ልብሴነው መሥፍን እና ወይዘሮ...
የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች በምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤቶችን እየተመለከቱ ነው።
ባሕርዳር፡ግንቦት 25/2018 ዓ.ም(አሚኮ) አሚኮ በባሕርዳር ከተማ ባካሄደው ምልከታ በየምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የድምጽ ውጤቶች ተለጥፈው ነዋሪዎች እየተመለከቱ ነው።
ውጤቶቹ ለማኅበረሰቡ በግልጽ በሚታዩ ቦታዎች ነው የተለጠፉት።
#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_ውጤት #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን...







