“ማንም ይመረጥ ማን የሕዝብ ድምጽ ማክበር ይገባል” የቆቦ ከተማ ነዋሪዎች

10

 

ወልድያ፡ ግንቦት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ምርጫ ክልል በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤት ለሕዝብ ይፋ እየተደረገ ይገኛል።

የምርጫ ጣቢያዎችን ጊዜያዊ ውጤት ሲመለከቱ አሚኮ ያገኛቸው የቆቦ ከተማ ነዋሪዎች ምርጫው ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ ኾኖ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አጠቃላይ ውጤቱን እስከሚያሳውቅ ድረስ በትዕግሥት እንደሚጠብቁ ጠቁመው “ማንም ይመረጥ ማን የሕዝብ ድምጽ ሊከበር ይገባል” ብለዋል።

የምርጫውን ውጤት በጸጋ መቀበል ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ግድ መኾኑንም ነው ነዋሪዎቹ ያስረዱት።

ከምርጫው በኋላ ከሚመሠረተው መንግሥት ጋር ሕዝቡ በልማት እና በሰላም ዙሪያ ተባብሮ መሥራት እንዳለበትም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_ውጤት #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየወልድያ ከተማ ነዋሪዎች ጊዜአዊ የምርጫ ውጤት እየተመለከቱ ነው።
Next articleበሺዎች የሚቆጠሩ ሕጋዊ ድረ ገጾች በመጠለፋቸው ተጠቃሚዎች ለሳይበር ጥቃት እየተጋለጡ ነው።