
ወልድያ፡ግንቦት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በወልድያ ከተማ ምርጫ ክልል በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ውጤቶች እየተገለጹ ይገኛሉ።
የወልድያ ከተማ ነዋሪዎችም ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶችን በየምርጫ ጣቢያዎቹ እየተመለከቱ ነው።
አሚኮ በከተማዋ ተዘዋውሮ በተመለከተባቸው የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ ቆጠራ ጊዜያዊ ውጤቶች ግልጽ በኾነ ቦታ ተለጥፈው ሕዝቡ እየተመለከታቸው መኾኑን ታዝቧል።
#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_ውጤት #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
