“ትግላችን ተጠልፎ ለጥፋት ኃይሎች መጠቀሚያ በመኾኑ ወደ ሰላም ተመልሰናል” የቀድሞ ታጣቂዎች

22

በደቡብ ጎንደር ዞን የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሣሪያቸውን ገቢ ያደረጉ የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመቀላቀል የሚያስችላቸውን ሥልጠና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

የታጣቂዎቹ መሪ ኾነው የቆዩት ወጣት ምትኩ ልጃለም እና ወጣት ክንዳለም ድረስ እንደገለጹት የቀደመ ትግላቸው የማንነት እና የወሰን ጥያቄዎች በሕግ የጸኑ ኾነው እንዲመለሱ እንጂ ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመተባበር ሀገር ለማፍረስ አልነበረም። ትግሉ ተጠልፎ ለሌሎች ጠላቶች የጥፋት አጀንዳ መጠቀሚያ በመኾኑ ወደ ሰላም መምጣታቸውንም ጠቅሰዋል።

በሕገ ወጡ ሕወሃት የተፈጸሙ በደሎች ሳይረሱ ከዚህ ጠላት ጋር መተባበር ትልቅ የታሪክ ስህተት መኾኑንም ገልጸዋል።

የደቡብ ጎንደር ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ጌትነት በዛ እንዳሉት የጥፋት ቡድኑ ዓላማ ሀገር ማፍረስ እና ፕሮጀክቶችን ማስተጓጎል መኾኑን በመረዳት የጥፋት አጀንዳቸውን በጋራ እንደሚያከሽፉም ተናግረዋል።

የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ እና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መንበር ክፈተው ሥልጠናው ሰላምን በዘላቂነት ለማስፈን የሚሰጥ መኾኑን ጠቁመዋል።

በጫካ የሚንቀሳቀሱ ሌሎች አካላትም የሰላም አማራጭን እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።

#አሚኮ #ሰላም #ኢትዮጵያ 🇪🇹

#ደብረ_ታቦር #መስከረም_14_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ተፈጥሯዊው የኢትዮጵያ አምባሳደር”
Next articleየኢትዮጵያ-ጅቡቲ የነዳጅ ምርቶች ማስተላለፊያ መስመር ኢትዮጵያንና ጅቡቲን የሚያገናኝ ስትራቴጂካዊና ድንበር ተሻጋሪ የመሠረተ ልማት