
ውጥን ሲሆን፤ ዓላማውም የኢትዮጵያን የኃይል ዋስትና ማሻሻል፣ ቀጣናዊ የንግድ ትስስርን ማሳደግ፣ እንዲሁም የነዳጅ ምርቶችን ከጅቡቲ ወደ
ኢትዮጵያ አስተማማኝ እና እምነት በሚጣልበት ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ማጓጓዝን ማረጋገጥ ነው። ይህ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል በሚደረግ የጋራ ኢንቨስትመንት የሚከናወን ነው።
ከጅቡቲዋ ዳመርጆግ እስከ ኢትዮጵያዋ ደወሌ ባለው መስመር ላይ ወደ 120 ኪሎ ሜትር ያህል የሚዘልቀው ይህ ፕሮጀክት፤ በዳመርጆግ
የሚገኙትን የባሕር ላይ ነዳጅ መቀበያና የባሕር ዳርቻ ማከማቻ ተቋማትን በደወሌ ከሚገኙት የሀገር ውስጥ ማከማቻና ማከፋፈያ ተቋማት ጋር
የሚያገናኝ የተቀናጀ የነዳጅ ሎጅስቲክስ ሥርዓት ይዘረጋል። በዳመርጆግ ተርሚናል ላይ የተጣሩ የነዳጅ ምርቶች ወደ ተዘጋጁ ልዩ ማከማቻዎች
የሚዘዋወሩ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎ በኢትዮጵያ በስፋት እንዲሰራጩ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት በሚሰጥ የነዳጅ ቱቦ አማካኝነት ወደ ደወሌ ይጓጓዛሉ።
