የተረጂነትን አስተሳሰብ በማስቀረት ዜጎችን ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር እየተሠራ ነው።

17
‎የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር «ከተረጂነት ወደ ምርታማነት» በሚል መርህ በከተማዋ የተለያዩ የሰብል ልማት እና የእንስሳት ርባታ ሥራዎችን እያከናወነ ነው።
‎በግብርና ዘርፍ በተለይም በበቆሎ ምርት የተሰማሩ ዜጎች በተደረገላቸው ድጋፍ ከተረጂነት ወጥተው ወደ ዘላቂ የገቢ ምንጭ መሸጋገራቸውን ገልጸዋል።
‎በብልጽግና ፓርቲ የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ አበባው ግዛቸው ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ፣ በጎዳና ሕይወት የቆዩ እና ተጋላጭ የኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በቋሚ የሥራ እና የገቢ ምንጭ በማሰማራት ከተረጂነት እንዲወጡ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
‎የአማራ ክልል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ፍቅሬ ሙሉጌታ በበኩላቸው በደብረ ማርቆስ ከተማ በምግብ ራስን የመቻል እና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች አበረታች መኾናቸውን ገልጸዋል።
‎በከተማ አሥተዳደሩ ተረጅነትን ለማስቀረት በሰብል ልማት፣ በእንስሳት እርባታ እና በሥራ ዕድል ፈጠራ የሚከናወኑ ሥራዎች የመስክ ምልከታ እና በተሠሩ ሥራዎች ላይ ውይይት ተካሂዷል።
‎
‎በመስክ ምልከታው የአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ምክትል ቢሮ ኀላፊ ንጹሕ ሽፈራውን ጨምሮ ሌሎች የክልል የሥራ ኅላፊዎች የሥራ ጉብኝት አድርገዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየኢትዮጵያ-ጅቡቲ የነዳጅ ምርቶች ማስተላለፊያ መስመር ኢትዮጵያንና ጅቡቲን የሚያገናኝ ስትራቴጂካዊና ድንበር ተሻጋሪ የመሠረተ ልማት
Next article“ሁልጊዜም ከሕዝብ ጎን”