
የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ የ2019 ዓ.ም የበጋ መስኖ ልማት የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ ኀላፊ ቤዛዊት ጌታሁን ብሔረሰብ አሥተዳደሩ ለመስኖ ልማት ሰፊ ጸጋ ያለው እና ዓመቱን ሙሉ የሚፈስሱ በርካታ ወንዞች ባለቤት መኾኑን ተናግረዋል።
እነዚህን ጸጋዎች በአግባቡ በመጠቀም በበጀት ዓመቱ በአንደኛ እና ሁለተኛ ዙር የበጋ መስኖ ከ71 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት መታቀዱን ገልጸዋል። ከዚህ ውስጥ ከ19 ሺህ ሄክታር በላይ የሚኾነው በአዲስ መስኖ የሚለማ መኾኑን ነው ያነሱት።
በበጀት ዓመቱ ለበጋ ስንዴ ልማት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ የገለጹት ኀላፊዋ በመስኖ ከሚለማው መሬት ውስጥ 49 ሺህ ሄክተር የሚኾነው በስንዴ እንደሚለማም ገልጸዋል። በምርት ዘመኑ ከመስኖ ልማቱ ከ7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃልም ብለዋል።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋሁን ተሰማ የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት ማረጋገጥ የሚቻለው የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የመሬት የማምረት አቅምን ማሳደግ ሲቻል መሆኑን ተናግረዋል።
በምርት ዘመኑ የተያዘውን የመስኖ ዕቅድ ለማሳካት በየደረጃው ያለው የአመራር ስምሪት ዋነኛ የትኩረት መስክ ኾኖ እንደሚሠራም ገልጸዋል።
የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አየን ብርሃን የአርሶ አደሮችን የዳበረ ልምድ ከጸጋዎች ጋር በማቀናጀት ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የውኃ አጠቃቀም ፍትሐዊነትን ማረጋገጥ፣ ብክነትን መቀነስ እና ሳይንሳዊ አሠራርን መከተል ያስፈልጋልም ነው ያሉት።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#እንጅባራ #ጥቅምት_14_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ !
