
የምሥራቅ ዕዝ ኮር የሠራዊት አባላት በምዕራብ ጎጃም ዞን ለሚገኙ አረጋውያን ማኅበር አባላት የ107 ሺህ 900 ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።
በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሥራ ኀላፊ የኾኑት ኮሎኔል ሬድዋን ሬባቶ ሠራዊቱ የሀገርን ሰላም እና ደኅንነት ከመጠበቅ ባሻገር ለወገናቸው የቆሙ እና ለሀገር ትልቅ ውለታ የዋሉ አረጋውያንን መደገፍ የማኅበራዊ ኀላፊነት አንዱ አካል ነው ብለዋል።
የኮሩ ሠራዊት ሁልጊዜም ከሕዝብ ጎን በመቆም አጋርነቱን የሚያሳይ እና ተግባራዊ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የገለጹት።
የምዕራብ ጎጃም ዞን የአረጋውያን ማኅበር ሠብሣቢ በፍቃድ ዲስሳ ሠራዊቱ ላደረገው በጎ እና አርዓያነት ያለው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የሀገር ድንበር እና ሰላም የሚያስከብረው ሠራዊት በችግር ውስጥ ያሉ አረጋውያንን በማሰብ ላደረገው እገዛ ማኅበሩ ትልቅ ክብር እና አድናቆት እንዳለው ነው የተናገሩት። ይህ ድጋፍ ለአረጋውያኑ ትልቅ ሞራል እንደሚኾናቸውም አንስተዋል።
መረጃው የምሥራቅ ዕዝ ነው።
#አሚኮ #DefenceNews #Ethiopia
#ባሕር _ዳር #መስከረም_14_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
