
ደብረ ታቦር: ግንቦት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የድምጽ ውጤት ይፋ አድርገዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎችም በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ጊዜያዊ የድምፅ ውጤቶችን እየተመለከቱ ነው።
ውጤቱን ሲመለከቱ ካገኘናቸው መካከል አቶ ልብሴነው መሥፍን እና ወይዘሮ እናንዬ ፈንታዬ የተካሄደው ምርጫ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንደነበር አንስተዋል።
ማኅበረሰቡ ከምርጫ ማግሥት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚያሳውቀውን ውጤት በጸጋ ተቀብሎ እና ከአሸናፊው ጎን ኾኖ ለሀገር ሰላም እና ልማት መሥራት አለበት ነው ያሉት።
ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ፓርቲዎች በሰላማዊ መንገድ ሀገራቸውን ማስቀጠል እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
ለኢትዮጵያ የሚገባትም ኾነ ለሕዝብ የሚበጀው ሰላማዊ ሂደት ነው ብለዋል።
#አሚኮ_ዜና #ምርጫ_2018
#ደብረታቦር_አማራ #ኢትዮጵያ🇪🇹
ዘጋቢ፦ አድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጅታል ሚዲያ ቤተሰብ ይኹኑ !
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
