
አዲስ አበባ: ግንቦት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምርጫ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው። የሕዝብን ሉዓላዊነት በተግባር የሚያሳይ፤ ሥልጣን በሰላማዊ መንገድ የሚሸጋገርበት እና የዜጎች ተሳትፎ የሚረጋገጥበት ሂደትም ነው።
ዜጎች መሪዎቻቸውን በመምረጥ የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው እንዲወስኑ የሚያስችል መሣሪያም ነው።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ መንግሥት የሚመረጠው በሕዝብ ፈቃድ ብቻ መኾኑን የተማርንበት መኾኑን የተናገሩት የፖለቲካል ሳይንስ ተመራማሪው ሽመልስ ኃይሉ ናቸው። ኢትዮጵያ በታሪኳ የተለያዩ የፖለቲካ ሁነቶችን አሳልፋለች የሚሉት የፖለቲካል ሳይንስ ተመራማሪው ሕዝቡ በምርጫ የመጣ መንግሥት እንዲመራው እንጂ ሌሎች አማራጮችን እንደማይፈልግ በጽናት ቆሞ መምረጡ ማሳያ ነው ብለዋል።
ሥልጣን የሚይዘው አካል ደግሞ የሕዝቡን ፍላጎት ማክበር እና አንድነቷ የተጠበቀች ኢትዮጵያን እንዲያስቀጥል ሕዝባዊ ኀላፊነት ተጥሎበታል ነው ያሉት።
ብልሹ አሠራሮችን መታገል የተመራጩ አካል የትኩረት አቅጣጫ ሊኾን ይገባል ሲሉም መክረዋል።
ዘጋቢ፦ አየለ መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
