ማኅበረሰቡ በምርጫው ያሳየው ንቁ ተሳትፎ የዴሞክራሲያዊ ልምምዱን ዕድገት የሚያሳይ መኾኑን የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

7

 

ጎንደር፡ግንቦት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ በኾነ መንገድ መጠናቀቁን የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱም ካለፉት የምርጫ ጊዜያት የተሻለ እና የሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ልምምድ ያደገበት መኾኑን መታዘባቸውንም ገልጸዋል።

ለሥልጣን ሽግግር የድምጽ ብልጫ እንጂ የኀይል አማራጭ ማክተም እንዳለበት ተናግረዋል።

ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት አቶ እሸቴ ዓለማየሁ እና አቶ ገድሉ መኳንንት የምርጫው ሂደት ሥልጣን በኀይል አማራጭ ሳይኾን በድምጽ ብልጫ ብቻ የሚገኝበት ሥርዓት መኖሩን ያረጋገጠ ነው ብለዋል። ማኅበረሰቡ ያሳየው ንቁ ተሳትፎ የዴሞክራሲያዊ ልምምዱን ዕድገት የሚያሳይ መኾኑን ጠቁመዋል።

ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ አቶ አያናው ደረበ በሀገረ መንግሥት ምስረታ ላይ የዜጎች እያንዳንዱ ድምጽ ትልቅ ዋጋ እንዳለው የተረዱበት ምርጫ መኾኑን ገልጸዋል።

በቀጣይ በአሸናፊነት ሥልጣን የሚይዘው ፓርቲ የኢትዮጵያን ዕድገት ከማፋጠን ጎን ለጎን፤ በሀገሪቱ የሚስተዋሉ የሕግ አለመከበር ችግሮችን፣ ብልሹ አሠራርን፣ የዜጎችን ዝቅተኛ ገቢ ማሻሻልን እና ልማትን ማፋጠን ላይ በትኩረት መሠራት እንዳለበት አንስተዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_ውጤት #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ ደስታ ካሣ

የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየሚያሸንፈው ፓርቲ አንድነቷ የተጠበቀች ኢትዮጵያን እንዲያስቀጥል ሕዝባዊ ኀላፊነት ይጣልበታል።
Next articleየአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ የፈተና መስጫ ቀናትን ይፋ አደረገ።