🇪🇹 ኢትዮጵያ አዲስ ታሪክ በምክክር እየጻፈች ነው🕊️
የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ የጦርነት እና የትጥቅ ግጭት ማኅደር ኾኖ ቆይቷል። ትውልዶች የፖለቲካ ልዩነቶቻቸውን በጠመንጃ አፈሙዝ ለመፍታት ሲሞክሩ ዘመናት ተቆጥረዋል። ይህ የኅይል አካሄድ ሀገሪቱን ለከፋ የሰው ሕይወት መጥፋት እና ለሀብት ውድመት ዳርጓታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ...
“ቁስሎቻችንን በውይይት አክመን፣ የጸናች ሀገር እንገነባለን!”
"እኛ ኢትዮጵያውያን በሕግና ሥርዓት፣ በጀግንነትና በነፃነት አፍሪካን ያበራን የታላቅ ታሪክ ባለቤቶች ነን! በረዥሙ ታሪካችን ውስጥ፣ ልዩነቶችን ከኃይል ይልቅ በተለያዩ የሽምግልና ሥርዓቶች የመፍታት ጥልቅ ልምድ ያለን ሕዝቦች ነን።
ዛሬ ኢትዮጵያ እየመከረች ነው! ልጆቿ ከአራቱም አቅጣጫ ተሰባስበው...
🌍 “የኢትዮጵያ ሰላም፣ መረጋጋት እና አንድነት ለቀጣናው እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው” አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ
የኢትዮጽያ ሀገራዊ ምክክር እየተካሄደ ነው። በምክክር ሂደቱ ተገኝተው ቁልፍ መልዕክት ያስተላለፉት በአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና ደኅንነት ኮሚሽነር አምሳደር ባንኮሌ አዶዬ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ታሪካዊ መኾኑን ተናግረዋል። እንደ አፍሪካ ኅብረት የዚህ ታሪካዊ ምክክር...
“የእርስ በእርስ ግጭት ከውጭ ጠላት ጋር ከመዋጋት በላይ ጎጅ ነው” ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ
ታላቋ ኢትዮጵያ ሀገራዊ ችግሮቿን ትፈታ ዘንድ ሀገራዊ ምክክር እያካሄደች ትገኛለች።
በምክክር ጉባዔው ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት የናይጄሪያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት እና በአፍሪካ ኅብረት የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በታሪካዊው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ግብዣ ስለተደረገላቸውም አመስግነዋል።...
“ግጭት እና ስቃይ ማብቃት አለበት!” ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ.ር)
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ እየተካሄደ ነው። በጉባዔው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ.ር) በዓለም ታሪክ ውስጥ በግጭት የተሠራም ኾነ በግጭት ያተረፈ ሀገር የለም ብለዋል። የተሻሉ የሚባሉ ሀገሮች ከሁሉም በላይ ሀገራቸውን ስላስቀደሙ፣...








