🌍 “የኢትዮጵያ ሰላም፣ መረጋጋት እና አንድነት ለቀጣናው እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው” አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ

8

 

የኢትዮጽያ ሀገራዊ ምክክር እየተካሄደ ነው። በምክክር ሂደቱ ተገኝተው ቁልፍ መልዕክት ያስተላለፉት በአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና ደኅንነት ኮሚሽነር አምሳደር ባንኮሌ አዶዬ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ታሪካዊ መኾኑን ተናግረዋል። እንደ አፍሪካ ኅብረት የዚህ ታሪካዊ ምክክር አካል በመኾናቸው እንደሚኮሩም ገልጸዋል። የምክክሩን ጥልቀት፣ ስፋት እና ጥንካሬውን እንደሚያደንቁም ገልጸዋል። በምክክር ሂደቱ እየተሳተፉ የሚገኙ ተሳታፊዎች ይህን ምክክር ኅብረቱ እንደሚደግፍ ያውቃሉም ብለዋል።

ሀገራዊ ምክክሩ ትልቅ እድል እንደኾነም አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ሰላምን እንደምታዘልቅ፣ ለውጥን እና እድገትን እንደምታመጣ የሚያሳይ ነውም ብለዋል። ይህ ምክክር የሀገራዊ ኀላፊነት መገለጫ እንዲሁም ሰላማዊ መፍትሔዎችን የማምጣት መተማመኛ መኾኑንም ገልጸዋል። ምክክሩ አካታች የኾነ እና ብዝኀነት ያለው እንደኾነም ጠቁመዋል።

📌 አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ እንዳሉት የምክክር ሂደቱ የሀገሪቱን ብዝኅነት የሚወክል እና አካታች መኾኑ የሂደቱን ጥንካሬ ያሳያል። ለተሳታፊዎችም የአፍሪካ ኅብረት ለዚህ ሂደት ሙሉ ድጋፍ ያለው መኾኑን ገልጸዋል።

👉 ይህ ታሪካዊ አጋጣሚ ኢትዮጵያ ሰላምን እንደምታዘልቅ፣ ለውጥን እና እድገትን እንደምታመጣ ማሳያ ከመኾኑም በላይ የሀገራዊ ኀላፊነት መገለጫ መኾኑን አንስተዋል።

👉 ኅብረቱ ሙሉ በሙሉ በራሳቸው በኢትዮጵያውያን የሚመራውን እና የሀገራዊ ባለቤትነት ስሜት ያለውን ይህንን የሰላም ጉዞ ያለምንም ማመንታት እንደሚደግፍ ገልጸዋል።

👉የኢትዮጵያ ሰላም፣ መረጋጋት እና አንድነት ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይኾን ለአጠቃላይ የአፍሪካ ቀጣና እጅግ ወሳኝ እና ስልታዊ ጠቀሜታ ያለው መኾኑንም ተናግረዋል።

👉የአፍሪካ ኅብረት ከ1963 ዓ.ም ጀምሮ ዋና መቀመጫውን በኢትዮጵያ ማድረጉን በኩራት የጠቀሱት አምባሳደሩ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ህልም እንዲሳካ እና ከአፍሪካ የብልጽግና ጉዞ (አጀንዳ 2063) ጋር እንዲጣጣም ኅብረቱ ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆም አረጋግጠዋል።

ሰላምን ለማስረጽ፣ መግባባትን እና ዘላቂ ልማትን ለማምጣት በጋራ መግባባት፣ በታማኝነት እና በዴሞክራሲያዊ እሴቶች እና መርሆች ላይ ቆመን ከኢትዮጵያ ጎን እንሰለፋለንም ብለዋል አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ።

#አሚኮ #Ethiopia #National_Dialogue

#ባሕር_ዳር_ሐምሌ_8_2018_ዓ_ም

በሮዛ የሻነህ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“የእርስ በእርስ ግጭት ከውጭ ጠላት ጋር ከመዋጋት በላይ ጎጅ ነው” ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ
Next article“ቁስሎቻችንን በውይይት አክመን፣ የጸናች ሀገር እንገነባለን!”