“ይበጀናል” የሚሉትን በነጻነት እየመረጡ መኾናቸውን የእንጅባራ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
እንጅባራ፡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በእንጅባራ ከተማ የኮሶበር ምርጫ ክልል መራጮች ያለምንም ግፊት "ይበጀናል" የሚሉትን ፓርቲ በነጻነት እየመረጡ መኾናቸውን ገልጸዋል።
የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች በሕጉ መሠረት በማለዳው 12 ሰዓት ላይ...
ምርጫ የሥልጡን ማኅበረሰብ መገለጫ መኾኑን የጎንደር ከተማ መራጮች ተናገሩ።
ጎንደር፡ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጠዋት ወጥተው ይበጀናል ላሉት ድምፃቸውን መስጠታቸውን በጎንደር ከተማ የምርጫ ክልል 2 መራጮች ተናግረዋል።
አሚኮ ያነጋገራቸው ወይዘሮ ህድጃ ጥጋቡ በጠዋት ወጥተው ይበጀኛል ላሉት ድምፃቸውን መስጠታቸውንም ነው የተናገሩት።
ሃሳባቸውን ያጋሩን ሌላኛው መራጭ አቶ መኮንን...
ለሰባተኛ ጊዜ በምርጫ የተሳተፉት መራጭ በኮምቦልቻ
ደሴ፡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሙሉጌታ ጌጡ ይባላሉ፤ የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪ ናቸው።
በኮምቦልቻ ከተማ ቦርከና ክፍለ ከተማ አየር ማረፊያ ቀበሌ አየር ማረፊያ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ በምርጫ በመሳተፍ ለሰባተኛ...
ለሰባተኛ ጊዜ የመረጡት የ90 ዓመት ባለጸጋዋ እናት
ባሕር ዳር: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ምርጫ ክልል ጣና 02 ምርጫ ጣቢያ ሲመርጡ ያገኘናቸው የ90 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋዋ ምንትዋብ አዘነልኝ መብታቸውን መጠቀማቸውን ገልጸዋል።
ከዚህ በፊት በተካሄዱ ስድስት ምርጫዎች ላይ ተሳታፊ እንደነበሩም አስታውሰዋል። ዛሬም...
የአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች ድምጻቸውን እየሰጡ ነው።
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የሚገኙ መራጮች ከማለዳ ጀምረው ካርዳቸውን በመያዝ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች
በመሄድ ድምጻቸውን እየሰጡ ነው።
ነዋሪዎቹ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት እና ድምጻቸውን ለመስጠት ረጅም ሰልፎችን በመያዝ በዴሞክራሲያዊ ሂደቱ ላይ...








