የአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች ድምጻቸውን እየሰጡ ነው።
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ የሚገኙ መራጮች ከማለዳ ጀምረው ካርዳቸውን በመያዝ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች
በመሄድ ድምጻቸውን እየሰጡ ነው።
ነዋሪዎቹ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት እና ድምጻቸውን ለመስጠት ረጅም ሰልፎችን በመያዝ በዴሞክራሲያዊ ሂደቱ ላይ...
በነጻነት በካርዳቸው የሚፈልጉትን መምረጣቸውን የዳንግላ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
እንጅባራ፡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዳንግላ ከተማ ነዋሪዎች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጻቸውን እየሰጡ ነው።
የ87 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ አቶ አሊ ሙሳ እንዳሉት በነጻነት በካርዳቸው የሚፈልጉትን መርጠዋል። ምርጫውን በጉጉት ሲጠብቁት እንደነበር ገልጸው የሀገር ህልውና የሚረጋገጠው በምርጫ...
“ምርጫው የሀገሪቱ የቀጣይ እጣ ፈንታ የሚወሰንበት ነው” የአዴኃን ሊቀ መንበር ተስፋሁን ዓለምነህ
ባሕር ዳር: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) ሊቀመንበር እና በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሠብሣቢ ተስፋሁን ዓለምነህ በባሕር ዳር ምርጫ ክልል ፋሲሎ 03 ምርጫ ጣቢያ 2ሀ-1 ተገኝተው...
የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ ድምጽ ሰጡ።
የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ በባሕር ዳር ድምጽ ሰጥተዋል።
ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
“በመምረጤ ደስ ብሎኛል” የዕድሜ ባለጸጋዋ እማሆይ ስንታየሁ
ባሕር ዳር፡ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያውያን ነጋቸውን በካርዳቸው ለመወሰን እየመረጡ ነው።
እማሆይ ስንታየሁ ይባላሉ። የ72 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ናቸው።
በባሕርዳር ከተማ ሕዳሴ የምርጫ ጣቢያ ድምጽ ሲሰጡ ነው ያገኘናቸው።
በመምረጤ ደስ ብሎኛል፤ መምረጣችን ሰላምን ለማስቀጠል ነው ብለዋል።
ትውልዱ ሀገር...








