በነጻነት በካርዳቸው የሚፈልጉትን መምረጣቸውን የዳንግላ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

5
🇪🇹🗳️እንጅባራ፡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዳንግላ ከተማ ነዋሪዎች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጻቸውን እየሰጡ ነው።
የ87 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ አቶ አሊ ሙሳ እንዳሉት በነጻነት በካርዳቸው የሚፈልጉትን መርጠዋል። ምርጫውን በጉጉት ሲጠብቁት እንደነበር ገልጸው የሀገር ህልውና የሚረጋገጠው በምርጫ ካርድ ብቻ በመኾኑ ድምፄን ለአመንኩት ሰጥቼያለሁ ብለዋል።
ሌላኛው ድምጽ ሲሰጡ ያገኘናቸው አቶ ግርማ ተሻለ ለሀገር የሚበጀውን እንደመረጡ ገልጸዋል።
የምርጫ ሂደቱ ፍጹም ሰላማዊ፣ ነጻነት ያለው፣ ያለምንም ወከባ የሚፈልጉትን የመረጡበት ስለመኾኑም ጠቁመዋል።
ሌሎች የከተማ ነዋሪዎችም ይጠቅመኛል፣ ይበጀኛል፣ ያስተዳድረኛል ያሉትን በካርዳቸው መምረጣቸውን ለአሚኮ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦አዳሙ ሽባባው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ምርጫው የሀገሪቱ የቀጣይ እጣ ፈንታ የሚወሰንበት ነው” የአዴኃን ሊቀ መንበር ተስፋሁን ዓለምነህ
Next articleየአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች ድምጻቸውን እየሰጡ ነው።