
ባሕር ዳር: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) ሊቀመንበር እና በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሠብሣቢ ተስፋሁን ዓለምነህ በባሕር ዳር ምርጫ ክልል ፋሲሎ 03 ምርጫ ጣቢያ 2ሀ-1 ተገኝተው ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
እርሳቸው ተገኝተው በመረጡበት ምርጫ ጣቢያ ዜጎች መብታቸውን ለመጠቀም ያላቸውን ተነሳሽነት መመልከታቸውን ገልጸዋል።
“ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የቀጣይ የሀገር እጣ ፈንታ የሚወሰንበት ነው፤ ተራ ሁነት አይደለም” ነው ያሉት።
ረጃጅም ሰልፎችን መመልከት ዜጎች ለዴሞክራሲ ልምምድ ተሳትፎ እያደረጉ መኾኑን ማሳያ ነው ብለዋል ሠብሣቢው።
#Ethiopian-electio #ኢትዮጵያ-ትመርጣለች
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
