
እማሆይ ስንታየሁ ይባላሉ። የ72 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ ናቸው።
በባሕርዳር ከተማ ሕዳሴ የምርጫ ጣቢያ ድምጽ ሲሰጡ ነው ያገኘናቸው።
በመምረጤ ደስ ብሎኛል፤ መምረጣችን ሰላምን ለማስቀጠል ነው ብለዋል።
ትውልዱ ሀገር ሰላም እንዲኾን መሥራት አለበትም ነው ያሉት። እኛ የምንፈልገው ሀገር ሰላም እንዲኾን፣ በሰላም ሠርተን እንድንኖር ነው ብለዋል።
ከአሁን ቀደምም በነበሩ ምርጫዎች ተሳትፎ እንደነበራቸው ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
