
ባሕር ዳር: ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ ምርጫ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የኾኑት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባሕር ዳር ከተማ ድምጽ ሰጥተዋል። በኢትዮጵያ ምርጫ እየተካሄደ ነው፤ እኛም በባሕር ዳር ከተማ ድምጻችን ሰጥተናል ብለዋል።
ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለማጽናት እና ቅቡልነት ያለው መንግሥት ለመመስረት ወሳኝ ተግባር ነው ብለዋል። ሕዝቡ ከምዝገባ ጀምሮ ለምርጫው ያደረገው ተሳትፎ የሚገርም መኾኑንም ገልጸዋል። ሕዝቡ ለዴሞክራሲ ላደረገው ተሳትፎም ምስጋና አቅርበዋል።
ሕዝቡ ከሌሊት ጀምሮ ለምርጫ መሰለፉንም አንስተዋል።
ምርጫ ቦርድ የገነባውን አቅም አድንቀዋል። ሕዝብ የመረጠውን እንቀበላለን፤ አንድ ፓርቲ ከሀገር በላይ አይደለም፤ ዋናው ነገር የሀገር ቀጣይነት ነው ብለዋል። ሕዝቡ ለሀገር ግንባታ ይኾናል የሚለውን ወኪል በነጻነት መምረጥ እንደሚችልም አንስተዋል።
ዘጋቡ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ !
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
