ዓባይን በስኬት አጠናቅቀናል፤ ወደ ቀይ ባሕር ተመልሰናል !

የኢትዮጵያ ታሪክ ከዓባይ እና ከቀይ ባሕር ጋር የተሳሰረ ነው። የዓባይ እናት ኢትዮጵያ የቀይ ባሕርን ታሪክም ከእርሷ ነጥሎ ማየት አይቻልም። ነገር ግን ታሪካዊ ጠላቶቿ እነዚህን የታሪኳ ማጠንጠኛ የኾኑ ውኃዎችን እንዳትጠቀም ብዙ ደባዎችን ሠርተዋል። አሁን ግን...

የጋራ ጥረት ለተሻለች ባሕርዳር!

የባሕር ዳር ከተማ ምክር ቤት አባላት፣ የከተማዋ ነዋሪ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች በከተማዋ የተሠሩ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። ጎብኝዎች የራቫል ብረታ ብረት ፋብሪካን፣ በድባንቄ ተራራ ላይ የተሠራ የእርከን ሥራ፣ የአጼ ቴዎድሮስ...

በአማራ ክልል ከ7 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅት እየተደረገ ነው።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ጌታቸው ቢያዝን የ2019 የትምህርት ዘመን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም የ2019 በጀት ዓመት የትምህርት ዘመንን ስኬታማ ለማድረግ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል። በየደረጃው ያሉ መምህራንን...

“ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ እና አስተማማኝ መሠረት ለመጣል የተቀናጁ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ” ምክትል...

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አረንጓዴ ዐሻራ - ተፈጥሮን ከመንከባከብ እስከ ሀገራዊ የምግብና ኢኮኖሚ ሉዓላዊነት የሚደርስ መኾኑን አንስተዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ችግኝ ከመትከል ወይም አካባቢን ከማስዋብ የዘለለ፣...

📌 ከአፈር ነዳጅ ለማዘጋጀት የተወጠነው ፈጠራ የት ደረሰ?

ከአስር ዓመታት በፊት በነዳጅ እና በሊቲየም ፈጠራ ሥራቸው የብዙዎችን ትኩረት ስበው የነበሩት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኬሚስትሪ መምህር እና ተመራማሪው አቡሃይ ውብሸት አሁን ፈጠራው ስላለበት ወቅታዊ ሁኔታ ከአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። እርሳቸው እና ሌሎች ጓደኞቻቸው...