13
🇪🇹🗳️
አዲስ አበባ፡ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢዜማ ፓርቲ መሪ እዮብ መሳፍንት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምጽ ሰጥተዋል።
የኢዜማው መሪ እስከአሁን የምርጫ ሂደቱ መልካም መኾኑን ገልጸው የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ማዕከላዊ የፓርቲ ቢሮ ማዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል።
እስከሁን በመላ ሀገሪቱ ባለው የምርጫ ሂደት ችግር እንዳላጋጠመ በሪፖርት አረጋግጠናልም ብለዋል።
ካርድ ይዞ ድምጽ አለመስጠት ትክክል አለመኾኑን የገለጹት የፓርቲው መሪ ሁሉም ዜጋ ካርዱን በአግባቡ አንዲጠቀምም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ ድምጽ ሰጡ።
Next articleአቶ አደም ፋራህ ድምጻቸውን ሰጡ።