
#አዲስ_አበባ: ሰኔ 26/2018 ዓ.ም ከአምስት ዓመታት በፊት የተመሠረተው ዘምዘም ባንክ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ ባንክ ነው።
በበጀት ዓመቱ ባንኩ ተደራሽነቱን በማስፋት እና የዲጂታል አሠራሮችን በመከተል ውጤታማ መኾኑን የዘምዘም ባንክ ሥራ አሥፈጻሚ መሊካ በድሪ አስታውቀዋል።
የደንበኞቹን ቁጥር 973ሺህ በማድረስ ቅርንጫፎቹንም ወደ 130 አሳድጓል ነው ያሉት።
የባንኩ የደምበኞች የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከነበረበት 11 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በ81 በመቶ ጭማሪ ወደ 21 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 29 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር መድረሱንም አስታውቀዋል።
ባንኩ ቀልጣፋ እና አስተማማኝ ግብይትን ለማስፈን የሰነድ መዋለ ንዋይ ምዝገባ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በማከናዎን አክሲዮኖቹን መሸጥ የሚያስችለው ምዕራፍ ላይ መገኘቱን የባንኩ ሥራ አሥፈጻሚ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል ራሄል ካሳ ዘምዘም ባንክ የሰነድ መዋዕለ ንዋይ ምዝገባ ማድረጉ የፋይናንስ ሥርዓቱን በማዘመን በካፒታል ገበያው ያለውን ሚና ያሳድጋል ብለዋል።
ባንኩ በገበያው ዋጋቸው 6 ቢሊዮን የሚኾኑ አክሲዮኖችን ለሽያጭ ማቅረቡ ተገልጿል።
#አሚኮ_ዜና #AMECO #ዘምዘምባንክ
ዘጋቢ: ሰላማዊት ነጋ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
