“በሀረሪ ክልል በማዕድን ዘርፍ ላይ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል” ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ

3
ባሕር ዳር: ሰኔ 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሀረሪ ክልል በማዕድን ዘርፍ ላይ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገልጸዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ እና ካቢኔያቸው በክልሉ በማዕድን ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በጉብኝታቸው ወቅትም ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን እንዳሉት
በክልሉ በማዕድን ዘርፍ ላይ በተለይም በግራናይት እና ላይምስቶን ምርት ያለውን እምቅ ሀብት ጥቅም ላይ በማዋል ረገድ አበረታች ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
እየተሠሩ በሚገኙ ሥራዎች በርካታ ዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ነው የተናገሩት።
በዘርፉ ያለውን ሀብት በአግባቡ መጠቀም ለዜጎች ተጠቃሚነት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መኾኑን ጠቁመው ጅምር ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በትኩረት ይሠራልም ብለዋል።
በክልሉ በማዕድን ዘርፍ የተሰማሩ አልሚዎችን ከማበረታታት ባሻገር በዘርፉ ለሚሰማሩ አዳዲስ ባለሀብቶች አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ነው ርእሰ መሥተዳድሩ የተናገሩት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየምድርን ጤና ከመጠበቅ አልፎ የምግብ ሉዓላዊነትን እስከማረጋገጥ የገዘፈው የአረንጓዴ አሻራ ጉዞ
Next articleአረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ አርዓያ እንድትኾን አድርጓታል።