“ማይካድራ፡- የማይረሱ ቀኖች፤ የማይዘነጉ ግፎች”
ባሕር ዳር: ኅዳር 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የማይረሱ በደሎች ደረሱባት፤ ለጀሮ የሚከብዱ ግፎች ተፈጸሙባት፤ ንጹሐን ያለ ጥላ እና ከለላ ተሰቃዩባት፤ ማንነታቸው እየተለዬ የመከራ ጽዋ ተጎነጩባት፤ እንደ ቅጠል ረገፉባት፤ አንጀት የሚያንሰፈስፍ የመከራ ድምጽ አሰሙባት፤ ደማቸውን አፈሰሱባት፤...
ከአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት በክልሉ ወቅታዊ የሰላም ጉዳይ የተላለፈ መልእክት፦
ሙሉ መልእክቱ ቀጥሎ ቀርቧል
ሰላም እስትንፋሳችን ነው!
ሰላም የዛሬውም ሆነ የወደፊቱ የትውልድ የኅልውና መሠረት ነው። የዛሬ አሻራ የሚኖረው በዛሬ ሰላማችን ልክ ነው። የትኛውም አካል ሰላም ከሌለ ስለዛሬ መኖሩን እንጂ ስለነገ እድገትና ልማት ሊያስብ አይችልም። የነገ መሠረትና...
“በምንም ዓይነት ሁኔታ፣ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ለሁሉም ፍጥረት ሰላም አስፈላጊና ወሳኙ ጉዳይ ነው፤ ...
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ ሰላምን ከመፍጠርና ከመገንባት ጋር የተያያዙ አጀንዳዎች የጋራ ጉዳዮች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
የሰላም ምሰሶ መሰረት የሚቀመጠውም ሆነ የሚፀናው...
በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጉህዴን ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ተመለሱ።
ባሕር ዳር: ኅዳር 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዞኑ የማንዱራ ወረዳ በጫካ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጠቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላም ተመልሰዋል።
በማንዱራ ወረዳ ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭ ተቀብለው ሲገቡ የዞኑ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችና...
“ጉራሽ ፈላጊ ጎሮሮዎች፣ እጅ ተመልካች ዓይኖች”
ባሕር ዳር: ኅዳር 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አርሰው የሚጎርሱት፣ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የሚተርፉት፣ የተራበን የሚያበሉት፣ የተጠማን የሚያጠጡት፣ የታረዘን የሚያለብሱት፣ ከጎተራቸው የማያጡት፣ ከመሶባቸው የማያጎድሉት ዛሬ ላይ ሁሉን አጥተዋል፡፡ ወደ ጎተራቸው የሚወርድ እህል ተቸግረዋል፤ በሞሶባቸው የሚሞላ እንጀራ...








