
የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የሕዝብ ግንኙነት እና ተሳትፎ ኀላፊ አድገህ መኩሪያ ለአሚኮ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት ፋብሪካው የነበረበት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር ተቀርፎለታል ብለዋል።
ለፋብሪካው የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያቀርበው የኃይል ማስተላለፊያ ተከላ ተጠናቅቆ ወደ ፋብሪካው ኃይል መለቀቁን ገልጸዋል።
ይህንን ተከትሎም ለፋብሪካው ስኳር ምርት ግብዓት የሚኾነው ሸንኮራ አገዳ ከቅጠሉ ለማለያየት የሚያስችለውን አገዳ የማቃጠል እና የማዘጋጀት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በጥቂት ቀናት ውስጥም ፋብሪካው ስኳር ማምረት እንደሚጀምር ኀላፊው አረጋግጠዋል።
ከ24 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሚጠቀመው ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ በቀን 12 ሺህ ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም አለው ነው ያሉት። ለ23 ሺህ ዜጎችም የሥራ ዕድል መፍጠር የሚችል ግዙፍ ፕሮጀክት እንደኾነም ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
See less
