“የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር እድገት መደላድል ነው” የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ታየ አጽቀሥላሴ

11
አዲስ አበባ፡ ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 4ኛው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ አራተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል።
የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ታየ አጽቀሥላሴም ኤክስፖውን ጎብኝተዋል። ፕሬዝደንት ታየ አጽቀሥላሴ የአንድ ሀገር የዕድገት መደላድል የኢንዱስትሪ ዘርፉ እንደኾነ ተናግረዋል።
በዚህ ኤክስፖም ይህንን የሀገር ውስጥ የማምረት አቅም አይተናል ብለዋል። ችግር ፈች የኾኑ ምርቶችም እየተመረቱ ስለመኾናቸው አንስተዋል።
ለእነዚህ ምርቶች ደግሞ የገበያ ትስስር መፍጠር፣ የተቋማት ትስስር እና ድጋፍ ያስፈልጋል ነው ያሉት።
በዘንድሮው የአራተኛው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖም ከ186 በላይ ኢንዱስትሪዎች ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አሥተዳደሮች ተሳትፎ አድርገዋል።
በኤክስፖው ከዚህ በፊት ያልነበሩ ግብዓቶች መቅረባቸው ተገልጿል።
ዘጋቢ፦ ኤልሳ ጉዑሽ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) በተገኙበት ሀገራዊ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
Next articleጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የኃይል አቅርቦት ችግሩን ቀርፎ ወደማምረት ሊገባ ነው።