
አዲስ አበባ: ግንቦት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድህረ ምርጫ ሂደት ተግባራትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
ከምርጫው ዕለት ጀምሮ ከፓርቲዎች እና ከግል ተወዳዳሪዎች ቅሬታዎችን በመቀበል እያስተናገደ እንደኾነም በመግለጫው ተመላክቷል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ አብዛኛዎችን ቅሬታዎች በአግባቡ ለመፍታት እየሠሩ መኾናቸውን ገልጸዋል። ሌሎች ቅሬታዎችን ለመፍታት ደግሞ ገለልተኛ የሕግ ባለሙያዎች ጉባኤ መቋቋሙን አንስተዋል።
ቅሬታዎች ከፓርቲዎች እና ከግል እጩዎች የመጡ መኾናቸውን እና በቦርዱ የቅሬታ አፈታት ሥርዓት መሠረት ለመፍታት እየተሠራ ነው ብለዋል ሰብሳቢዋ።
ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ኃይለኢየሱስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
