825 የምርጫ ክልሎች የማዳመር ሥራዎችን ማጠናቀቃቸውን ቦርዱ አስታወቀ።

20

 

አዲስ አበባ: ግንቦት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ጀምሮ የምርጫውን ሂደት በመገናኛ ብዙሃን በኩል ለሕዝብ እያደረሰ ይገኛል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የውጤት ሂደቱን ተከትሎ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የምርጫ ክልሎች የማዳመር ሥራ ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ ተናግረዋል።

ከ1 ሺህ 138 የምርጫ ክልሎች ውስጥ 825 የምርጫ ክልሎች የማዳመር ሥራቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።

29 የሚደርሱ የምርጫ ክልሎች ደግሞ ወደ ማረጋገጫ ሂደት መግባታቸውን ሰብሳቢዋ ተናግረዋል።

ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ኃይለኢየሱስ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል “ኢትዮጵያ ታምርት” ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ነገ በኮምቦልቻ ከተማ ይካሄዳል።
Next articleቦርዱ ከፓርቲዎች እና ከግል እጩዎች የቀረቡ ቅሬታዎችን እያስተናገደ መኾኑን አስታወቀ።