የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በመጪው ሳምንት እንደሚጀመር ትምሕርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ባሕርዳር፡ ጥቅምት 13/2013 ዓ.ም (አብመድ) የ2012 ትምሕርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ከጥቅምት 16 እስከ 30 /2013 ዓ.ም በየትምሕርት ቤቶቹ እንደሚካሄድ የትምሕርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ እንደሚያመላክተው የፈተና ምዝገባ ሂደቱን...
የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በአንድ ክፍል እስከ 30 ተማሪዎችን ለማስተማር በሚደረገው ጥረት የመማሪያ ክፍል ጥበት፣...
ባሕርዳር፡ ጥቅምት 13/2013 ዓ.ም (አብመድ) በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን ትምህርት በሽታውን በመከላከል ለማስጀመር የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በትምህርት ዙሪያ ከሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ይልቃል...
756 የምግብ አይነቶችን መዝግቦ ለኅብረተሰቡ መረጃ ማቅረቡን የኢትዮጵያ የምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ባሕርዳር፡ ጥቅምት 13/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን በ2013 በጀት ዓመት ባለፉት ሦስት ወራት በምግብ ጥራትና ደኅንነት፣ በመድሀኒትና የህክምና መሳሪያዎች ጥራት ደኅንነትና ፈዋሽነት ላይ የተሰሩ የቁጥጥር ሥራዎችና የተወሰዱ እርምጃዎችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።
ባለስልጣን መሥሪያ...
በከተሞች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፣ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፡፡
ባሕርዳር፡ ጥቅምት 13/2013 ዓ.ም (አብመድ) በከተሞች ለሰላም እጦት መንስኤ የሆኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አስታወቁ፡፡
ፕሬዝዳንቷ ይህን ያስታዎቁት በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ባለው የከተሞች የሰላም ፎረም ላይ ነው፡፡ “የፍትህና ተጠያቂነት...
የጥሬ ቆዳና ሌጦ ምርትን ከብክነት ለመታደግ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 13/2013 (አብመድ) የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በበጀት ዓመቱ ከዘርፉ የውጭ ንግድ ገቢ 100 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ማቀዱን አስታውቋል፡፡ ባለፈው የክረምት ወራት የቆዳና ሌጦ ዋጋ በመውረዱ በተለይ ጥሬ ሌጦ በየሜዳው...








