🌱 ኢትዮጵያ በ2050 የካርቦን ልቀትን ዜሮ ለማድረስ በቁርጠኝነት እየሠራች ነው! 🌍

2

 

#አዲስ አበባ: ሰኔ 23/2018 የግብርና ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው “2ኛው ሀገራዊ የካርቦን ገበያ ሴሚናር” ተካሂዷል።

ውይይቱ የኢትዮጵያን የካርቦን አቅም እና የሽያጭ መጠን ለማሳደግ በሚያስችሉ ሥራዎች ዙሪያ ያተኮረ ነው።

ከመድረኩ የተደመጡ ዋና ዋና ነጥቦች፦

📉 የልቀት ቅነሳ ግብ፦ ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ያለውን 70 ነጥብ 3 በመቶ የሙቀታማ ጋዞች ልቀት በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ በ2050 ዓ.ም የካርቦን ልቀትን ሙሉ በሙሉ ዜሮ ለማድረስ እየሠራች መኾኑን የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዲኤታ ስዩም መኮንን ገልጸዋል።

🌳 የተከናወኑ ስኬታማ ተግባራት፦ ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ማሳያ ከኾኑት መካከል የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፣ የአረንጓዴ ከተሞች መፈጠር፣ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እና መሰል የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶች፤ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መግባት እና የሌማት ትሩፋት በዋናነት ተጠቃሽ ናቸው።

💰 የወደፊት ዕቅድ እና በጀት፦ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ የተቀመጡትን የልቀት ቅነሳ ግቦች ለማሳካት 106 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

🔬 ሳይንስ እና የካርቦን ገበያ፦ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ.ር) ካርቦን በሳይንሳዊ ጥንቃቄ ሊሸጥ የሚችል ትልቅ ሀብት መኾኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ የሳይንሱን ዓለም ዕውቀት መጠቀም ወሳኝ መኾኑንም አብራርተዋል።

👨‍🌾 ለአርሶ አደሮች የሚተርፍ ጥቅም፦

የግብርና ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር እያሱ ኤልያስ የካርቦን ሽያጭ ለአርሶ አደሮች ተጨባጭ ጥቅም የሚያስገኝ በመኾኑ ለዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት በር የሚከፍት ጠንካራ ብሔራዊ አቅም መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።

🔄 የጋራ ጥሪ፦

ይህንን ዘላቂ የአረንጓዴ ዕድገት ሽግግር ከግብ ለማድረስ በመንግሥት፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በግሉ ዘርፍ እና በልማት አጋሮች መካከል ጠንካራ ትብብር እንዲኖር ጥሪ ቀርቧል።

🇪🇹 ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት እና በአየር ንብረት ዲፕሎማሲ የአፍሪካ መዲና መኾኗን በተግባር እያረጋገጠች ነው። 🇪🇹

#አሚኮ_ዜና #የአየርንብረትለውጥ #የአረንጓዴአሻራ #የካርቦንገበያ #ኢትዮጵያ #GreenLegacy #Ethiopia #ClimateAction

ዘጋቢ፦ ሐናማርያም መስፍን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleአረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያን እየቀየረ ያለ ብሔራዊ የእድገት ጉዞ ነው። 🌿🇪🇹
Next articleየላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት በዓለም ከፍተኛ ተጓዦች ከተመረጡ የዩኔስኮ ምርጥ አምስት ቅርሶች መካከል ተካተቱ።