“ከአንድ ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቷል” የግብርና ሚኒስቴር
ባሕር ዳር: ኅዳር 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ለ2016/17 የምርት ዘመን ለመግዛት ከታቀደ 23 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ እስከ አሁን ከአንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን የግብርና ሚኒስቴር ገልጿል።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሶፊያ...
እንደ ሀገር የሰላም እሴቶችን መገንባት እና ሰላም እንዲረጋገጥ መሥራት ይገባል ተባለ።
አዲስ አበባ: ኅዳር 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የሰላም ምክር ቤት ሁለተኛ መድረክ እየተካሄደ ነው።
ከተመሠረተ ዘጠኝ ወራት ያስቆጠረው የሰላም ምክር ቤት የሰላም ግንባታ ሥራን ገምግሞ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ውይይት እያካሄደ ነው።
የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ስዩም መስፍን...
በትምህርት ዘርፉ የሚደረገው የማሻሻያ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተባለ።
ባሕር ዳር: ኅዳር 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ)32ኛው የትምህርት ጉባኤ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በእውቀት የበለጸገ ዜጋ ለመፍጠር በትምህርት ዘርፉ የሚደረገው የማሻሻያ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።
ሚኒስትሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት በትምህርት ዘርፉ የተሰራው...
ባለፉት አራት ወራት ከ193 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።
ባሕር ዳር: ኅዳር 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት አራት ወራት 193 ነጥብ 98 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታውቋል።
የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የሚሰበሰበው አጠቃላይ ገቢ ከዓመት ዓመት እያደገ መጥቷል።
ከሐምሌ 2015 ዓ.ም እስከ...
ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በፆታዊ ጥቃት ላይ በሚመክረው መድረክ ለመካፈል ደቡብ አፍሪካ ገቡ።
ባሕር ዳር: ኅዳር 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሰውን ፆታዊ ጥቃት ለማስቆም በሚመክረው ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ገብተዋል፡፡
ጉባዔው ትናንት የተጀመረ ሲሆን እስከዛሬ እንደሚቀጥል በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ...








