የኢትዮጵያን ከፍታ የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶች 

13

 

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብት የበለጸገች ታላቅ ሀገር ናት።

ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው ባላት ጸጋ ልክ መጠቀም ሳይችሉ ኖረዋል። በዚህም ምክንያት መበልጸግ ሲገባቸው በድህነት ውስጥ ለመኖር ተገድደው ቆይተዋል።

አሁን ግን የኢትዮጵያ የድህነት ምዕራፍ ሊዘጋ ነው። ጸጋዋ ለዓለም ሊገለጥ፤ የኢኮኖሚ ተደራሽነቷ በዓለም እንዲሠራፋ የሚያደርግ አዲስ ምዕራፍ ተጀምሯል! ✨

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ ባደረጉት ንግግር ጥቁሮች እንደምንችል እና እንደምናሳካ አሳይተናል ማለታቸው ይታወሳል።

ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚፈስባቸውን እና የአፍሪካውያንን አንገት ቀና የሚያደርጉ ሰባት ታላላቅ የ”ጉባ ብሥራት” ሜጋ ፕሮጀክቶችን በወቅቱ ይፋ አድርገዋል።

🚀 የትውልዱ ተስፋ የኾኑት ሰባቱ ሜጋ ፕሮጀክቶች፦

1️⃣ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ⚛️
2️⃣ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ 🌱
3️⃣ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ✈️
4️⃣ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካ
5️⃣ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ⛽️
6️⃣ የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ልማት ፕሮጀክት 🏢
7️⃣ የኮይሻ ሜጋ የኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ናቸው።

“ለኢትዮጵያ ነግቷል፣ኢትዮጵያ ከተረጅነት ወደ ረጅነት ትሸጋገራለች” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥቂት ዓመታት የጉባ ብሥራቶችን ለማጠናቀቅ ይሠራል ነበር ያሉት።

በጥቂት ዓመታት ውስጥ እነዚህን ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ በጋራ መቆም እንደሚገባም ማሳሰባቸው ይታወሳል።

የሜጋ ፕሮጀክቶቹ ዋና ዋና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎቻቸው፦

👉 የውጭ ምንዛሬን ማዳን እና የንግድ ሚዛንን ማሻሻል 💰
👉 የኢነርጂ እና የኃይል ዋስትናን ማረጋገጥ ⚡️
👉 ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር እና መሠረተ ልማትን ማስፋፋት
👉 የውጭ ኢንቨስትመንትን መሳብ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር በማምጣት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገትን ያረጋግጣሉ።

ሕዝቦቿ በሀገራቸው ሠርተው ስኬታማ እንዲኾኑ፣ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋ የተረጋገጠ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንድትኾን፣ ቀጣዩ ትውልድ የተረጋጋ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ኢኮኖሚ አቅም ያላት ሀገር እንዲኖረው ሜጋ ፕሮጀክቶቹ ጉልህ ሚና ይኖራቸዋል።

ከወራት በፊት በጉባ የተበሰሩት እነዚህ ሜጋ ፕሮጄክቶች ተጀምረዋል። ሥራቸው እየተካሄደ ነው። ፕሮጄክቶቹ ሲጠናቀቁ የኢትዮጵያን እድገት ከፍ ያደርጋሉ። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚውን ኢኮኖሚ ለመገንባት በትኩረት እየሠራች ነው።

💬 እነዚህ ሜጋ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ከኢትዮጵያውያን ምን ይጠበቃል ?

#Ethiopia #MegaProjects #(የጉባ ብሥራቶች)Guba #EconomicGrowth #Africa

ዘጋቢ:-ያየህ ፈንቴ

Previous article” የሰጣችሁን ጊዜ ያላሳካናቸውን እንድናሳካ፣ ያላደረስነውን ልማት እንድናዳርስ ቃል ኪዳናችንን የምናድስበት ነው” ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Next articleየቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ብልጽግና ፓርቲ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማሸነፉን ተከትሎ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፈ።