አርሶ አደሮች እና ከተሜው ስለ ምርጫው ተስፋም ሥጋታቸውን ተናገሩ፡፡
ባሕር ዳር፡- ጥር 15/2012ዓ.ም (አብመድ) ከሀገራዊ ምርጫው አስቀድሞ መሥተካከል ላለባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች መንግሥት ትኩረት እንዲሰጥ አስተያዬት ሰጪዎች ጠየቁ፡፡
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በወርሃ ነሃሴ ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን በጊዜያዊ መርሃ ግብሩ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ ምርጫው...
የጋሞ አባቶችና ወጣቶች በመላ ሀገሪቱ በመዘዋወር ስለ ሀገር አንድነት እና ሰላም ሊሠሩ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡- ጥር 14/2012ዓ.ም (አብመድ) በመላው ሀገሪቱ ያሉ ፖለቲከኞች ግጭት እንዳይቀሰቀስ እንዲሰሩ የጋሞ አባቶች ጠይቀዋል፡፡
ከአርባምንጭ ተነስተው መዳረሻቸውን ጎንደርን በማድረግ ጥምቀትን በጎንደር ታድመው፣ ስለፍቅርና አንድነት ሲመክሩ የሰነበቱት የጋሞ አባቶችና ወጣቶች ዛሬ ጥር 14/2012 ዓ.ም ባሕር...
መንግሥት የሀገሪቱን ወቅታዊ አሳሳቢ ሁኔታዎች ለይቶ እንዲያስተካክል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጠየቀ፡፡
በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብ እና የመደራጀት መብት በዋና ከተማዋ እና በክልሎች ውስጥ አልፎ አልፎ አላግባብ የመደናቀፍ ሁኔታ ስለተከሰተ መንግስት ማስተካከያ እንዲያደርግ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጠይቋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የሥራ...
ቋሚ ኮሚቴው የመንግሥታት ግንኙነት ሥርዓት ረቂቅ አዋጅ ዳግም እንዲታይ ወሰነ፡፡
ባሕር ዳር፡- ጥር 14/2012ዓ.ም (አብመድ) የመንግሥታት ግንኙነት ሥርዓት ረቂቅ አዋጅ ዳግም እንዲፈተሽ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ የፍትህና የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጠየቀ።
ቋሚ ኮሚቴው የመንግሥታት ግንኙነት ሥርዓት ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ትናንት ከባለድርሻ አካላት ጋር...
በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጸመ ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አረጋገጠ፡፡
ባሕር ዳር፡- ጥር 13/2012ዓ.ም (አብመድ) በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወምበራ ወረዳ ኮንግ ቀበሌ ማዕከል በተፈጸመ ጥቃት የሰዎች ሕይወት ማለፉን ፌዴራል ፖሊስ አረጋግጧል፡፡
ድርጊቱ የተፈጸመው ጥር 8/2012 ከቀኑ 10፡00 አካባቢ እንደሆነ ነው ነዋሪዎቹ እና የሥራ ኃላፊዎቹ የተናገሩት፡፡...







