የአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

7

 

📌 የሕክምና ትምህርትን በአፍሪካ ማስፋፋት እና የአህጉሪቱ የጤና ባለሙያዎች ትምህርት ላይ የሚያተኩረው የሕክምና ትምህርት (MedEd Africa 2026) አህጉራዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ከአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ቤቶች ጥምረት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ 2ኛው የ(MedEd Africa) ጉባኤ “የአፍሪካን የጤና ግብረ ኃይል ላልተረጋገጠ መጻኢ ጊዜ ማዘጋጀት፣ አጋርነትን፣ ቴክኖሎጂን፣ ፈጠራን እና አመራርን መጠቀም” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

🎯 የጉባኤው ዋና ዋና ትኩረቶች እና ዓላማዎች፦

ጥራት እና ትብብር፦ በአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ጥራትን ማሳደግ፣ አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከር እና ብቁ የሕክምና ባለሙያዎችን ማፍራት።

👉 የራስን ዕድል በራስ መወሰን፦

የሕክምና ትምህርትን ለማሳደግ የሚወጡ ፖሊሲዎች እና የገንዘብ ድጋፎች ከውጭ ዕርዳታ ጥገኝነት ወጥተው በአፍሪካ ሀገራት እና ተቋማት ሙሉ ባለቤትነት ላይ እንዲመሠረቱ ማድረግ።

ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ፦ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI)፣ የዲጂታል መድረኮችን እና በሲሙሌሽን የታገዙ የተግባር ልምምዶችን በጤና ትምህርት ውስጥ ማስፋፋት።

👉 ቅድሚያ የሚሰጡ ዘርፎች፦

የሕክምና ሥርዓተ ትምህርቶች የአህጉሪቱን ቀዳሚ የጤና ችግሮች በተለይም የእናቶች፣ የጨቅላ ሕጻናት እና የስነ ተዋልዶ ጤናን ታሳቢ ያደረጉ እንዲኾኑ ማስቻል።

የብቃት ማረጋገጫ፦ በአፍሪካ አገራት መካከል የሕክምና ትምህርት ምዘና እና የብቃት ማረጋገጫ (Accreditation) እርስ በእርስ የተጣጣመ እንዲኾን መንገድ መፍጠር።

👉 👥 ተሳታፊዎች፦

በዚህ ሰፊ አህጉራዊ መድረክ ላይ ከ46 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 117 ተቋማት ተወክለዋል። ከ750 በላይ የሕክምና ትምህርት ቤት ዲኖች፣ መምህራን፣ የጤና ፖሊሲ አውጭዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የሕክምና ተማሪዎች እና ዓለም አቀፍ አጋሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

✍️ ዘጋቢ፦ መሠረት መቅጫ

#አሚኮዜና #ጤና #ህክምና #MedEdAfrica2026 #Ethiopia #AddisAbaba #AfricaHealth #MedicalEducation #HealthcareInnovation
#አዲስ_አበባ_ሰኔ29_2018_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ ይገባል።