ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የጤናውን ዘርፍ ለማጠናከር ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ አፍስሳለች።

1
በአፍሪካ የጤና ባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ ያለመ ሁለተኛው አሕጉራዊ የሕክምና ትምህርት ጉባኤ 2026 የ46 ሀገራት ተወካዮች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተጀምሯል።
ጉባኤውን የከፈቱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ የዘረጋችው ሥርዓት ከራሷ አልፎ ሌሎች ሀገራት ተማሪዎች ዕድል በመስጠት ኢትዮጵያ እንደ ቀጣናዊ የልቀት ማዕከል እያገለገለች ትገኛለች ብለዋል።
በተጨማሪም የጤና ሥርዓቱን ከሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) እና ከዲጂታል ፈጠራ ጋር በማስተሳሰር ጥራት ላለው የጤና አገልግሎት ሰፊ ሥራ እየተሠራ መኾኑንም ጠቁመዋል።
ለዚህም ማሳያ የሚኾን በጤና ኢንፎርማቲክስ፣ በሮቦቲክስ እና በዲጂታል ምርመራ ላይ የሚያተኩር በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የኤአይ ዩኒቨርሲቲ ለመክፈት ዝግጅት እየተደረገ መኾኑንም አንስተዋል።
የአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ቤቶች ጥምረት ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ሊዮኔል ግሪን ቶምፕሰን የአፍሪካ የሕክምና ተቋማት ከውጭ ዕርዳታ ጥገኝነት ወጥተው የአህጉሪቱን ችግር በአፍሪካውያን መፍትሔ መቅረጽ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ሀገራት ሥርዓተ ትምህርታቸውን ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር ማጣጣም እንዳለባቸው ገልጸዋል። አሁን ላይ ዋነኛው ትኩረት ከቁጥር ወደ ጥራት መዞር እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ፦ መሠረት መቅጫ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleከኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እስከ ማኅበራዊ ደኅንነት
Next articleየአረንጓዴ አሻራ ትልቅ የኢኮኖሚ ምንጭ ኾኗል።