
በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ ተመዝግቧል። ሀገሪቱ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የጀመረችው የግብርናው ዘርፍ ሪፎርም ጉዞ ተረጅነትን የሚያስቀር ነው።
🎯 በግብርናው ዘርፍ ዕድገት ለማምጣት በሀገር ደረጃ በርካታ ርምጃዎች ተወስደዋል። ከፖሊሲ ማሻሻያ ጀምሮ የግብርና ሜካናይዜሽንን ማስፋፋት፣ የኩታ ገጠም አሠራርን መጠቀም፣ የግብዓት አቅርቦትን የገበያ ትስስር ማስፋፋት፣ እንዲኹም የተቀናጀ የመስኖ ልማትን ማዘመን በአብነት የሚጠቀሱ የሪፎርም ሥራዎች ናቸው።
ሀገሪቱ በወሰደችው የፖሊሲ አቅጣጫ እና ለዘርፉ በሰጠችው ልዩ ትኩረት የላቀ ውጤት እየተመዘገበ መምጣቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገልጸዋል።
✅ባለፉት አምሥት ዓመታት አጠቃላይ የግብርና ምርት ከ44 ሚሊዮን ቶን ወደ 150 ሚሊዮን ቶን አድጓል። በዚህም ከ3 እጥፍ በላይ የምርት ዕድገት አምጥቷል።
✅የዶሮ ስጋ ምርት ከ8 ሺህ ቶን ወደ 190 ሺህ ቶን ከፍ ብሏል። ይህም የ296 በመቶ ጭማሪ እንዳለ ያሳያል።
✅ በ2018 በጀት ዓመት 29 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማልማት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኩንታል ምርት ተሠብሥቧል።
✅ ቡናን ለውጭ ገበያ በማቅረብ በአንድ ዓመት ብቻ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት ተችሏል። ይህም የ17 ዓመታት የቡና ምርት ገቢን በአንድ ዓመት ማሳካት የተቻለበት ታሪካዊ ስኬት ኾኗል።☕💰
✅ቀደም ሲል ስንዴን ከውጭ በማስገባት በርካታ ዶላር ታወጣ የነበረውን ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ወደ ውጭ እየላከች የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ጀምራለች።
✅የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረው የሌማት ቱርፋት መርሐ ግብር አስገራሚ ውጤት ተገኝቶበታል።
✅የአቮካዶ፣ ሙዝ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ እና ሌሎችንም የፍራፍሬ አይነቶች በስፋት በማምረት ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ኾኗል። ለአብነትም በአቮካዶ ምርት በአፍሪካ ሁለተኛዋ ለውጭ ገበያ የምታቀርብ ሀገር መኾን ችላለች።
በግብርናው ዘርፍ የመጣው ለውጥ ለበለጠ ዕድገት የሚያነሳሳ ስለመኾኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።
📊ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበች ያለው ተጨባጭ ለውጥ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ እና የተረጅነት ታሪክን የመቀየር ግስጋሴዋን እንድታስቀጥል አስችሏታል።
#አሚኮ #Agriculture #Ethiopia🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መሥከረም _12_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ፦ አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
