በሆርሙዝ ሰርጥ ያለውን ውጥረት ለማርገብ ጥረት እያደረገች መኾኗን ኢራን ገለጸች።

3
ባሕርዳር፡ ግንቦት 07/2018ዓ.ም (አሚኮ) በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ያለው ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ አሁንም ዘላቂ እልባት አላገኘም።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጊቺ በሆርሙዝ የባሕር መስመር ዙሪያ ያለው ሁኔታ በጣም ውሥብሥብ መኾኑን ገልጸዋል። ቴህራን የውኃ መስመሩ ላይ ያለውን ውጥረት ለማርገብ ጥረት እያደረገች መኾኗን ገልጸዋል።
ከአሜሪካ ጋር የሚደረገው ድርድር ወደ መቀዛቀዝ ደረጃ መሸጋገሩን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። ዋሽንግተን ለጉዳዩ ያላትን ቁርጠኝነት እንደሚጠራጠሩም ተናግረዋል።
ኢራን ያከማቸችውን የበለጸገ ዩራኒየም ወደ ሩሲያ ለማዛወር ከሞስኮ ጋር መወያየቷንም አልጀዚራ አስነብቧል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን የኑክሌር መርሐ-ግብር ለ20 ዓመታት እንዲታገድ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። ስምምነቱ ተግባራዊ ሊኾን የሚችለው ግን የኢራን ቁርጠኝነት ዕውነተኛ መኾኑ ሲረጋገጥ ብቻ እንደኾነ አስጠንቅቀዋል።
ኢራን በበኩሏ የነዳጅ ማዕቀቦች እንዲነሱ እና ጦርነቱ በሁሉም ግንባሮች እንዲቆም ቅድመ-ሁኔታ አስቀምጣለች።
የአሜሪካ እና የቻይና መሪዎች የሆርሙዝ የነዳጅ መስመር ክፍት ኾኖ እንዲቆይ ቀደም ብለው መስማማታቸው ይታወሳል።
በስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleሕገ ወጥ የነዳጅ ዝውውር እና ግብይት የሚፈጽሙ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው።
Next articleብልጽግና ፓርቲ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሠራ ሀገራዊ ፓርቲ ነው።