
ከሚሴ፡ ግንቦት 07/2018ዓ.ም (አሚኮ) በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የገርቢ ክላስተር የብልጽግና ፓርቲ ደጋፊዎች እና አባላት የተሳተፉበት የምርጫ ቅስቀሳ እና የዕጩ ተመራጮች ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አህመድ አሊ ብልጽግና ፓርቲ ባለፈው ምርጫ ወቅት ቃል የገባቸውን በተግባር ያረጋገጠ ኅብረ ብሔራዊ ፓርቲ ነው ብለዋል።
የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች በመለየት ለመመለስ እየሠራ ያለ ፓርቲ እንደኾነም ጠቁመዋል።
እንደ ሀገር በርካታ ሀገራዊ ኢኒሼቲቮችን በመፍጠር በተሠራው ሥራ በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበ ፓርቲ መኾኑንም ጠቁመዋል።
የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ኹሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ አስረድተዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር ሥራዎችን በመሥራት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሠራ ሀገራዊ ፓርቲ መኾኑንም አስረድተዋል።
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
