የቅርሶች መመለስ ትውልዱ የራሱን ታሪክ እንዲጽፍ ያነሳሳሉ።

3
አዲስ አበባ: ግንቦት 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ዘለላ እና ሸማን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን እና የእንግሊዝ ሙዚየም ርክክብ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው የዘመናዊት ኢትዮጵያ መሃንዲስ እና የሀገር ኩራት የነበሩት ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ኢትዮጵያን በማሠባሠብ እና የሀገር እሳቤን በማዋለድ ረገድ ታሪካዊ አሻራን ጥለዋል ብለዋል።
በመቅደላ ጦርነት ተወስደው የነበሩ የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ዘለላ እና የሸማ ልብሳቸው በዲፕሎማሲያዊ ጥረት መመለሱንም ተናግረዋል።
የአማራ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ አየለ አናውጤ (ዶ.ር) ዳግማዊ ቴዎድሮስ የዘመናዊነት እና የአንድነት ምሳሌ ናቸው ብለዋል። ይህ ቅርስ ወደ ሀገር መምጣቱ ትውልዱ የራሱን ታሪክ እንዲጽፍ ለማነሳሳት ጉልህ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል።
የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ እና የሸማ ልብሶች ወደ ሀገር የተመለሱት በዲፕሎማሲያዊ ጥረት ነው ያሉት ደግሞ ዶክተር አሉላ ፓንክረስት ናቸው። የኢትዮጵያን እና የእንግሊዝን ሕዝብ ወዳጅነት የሚያጠናክር ትልቅ ስኬት ነውም ብለዋል።
ዘጋቢ፦ አየለ መስፍን
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleብልጽግና ፓርቲ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሠራ ሀገራዊ ፓርቲ ነው።