ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ላለማምረት ከአሜሪካ ጋር ከስምምነት ላይ ደረሰች።

5

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢራን ከአሜሪካ ጋር በደረሰችው የረቂቅ ስምምነት መሠረት የኑክሌር መሣሪያዎችን ላለማምረትም ኾነ ላለመታጠቅ መስማማቷን አንድ ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣን ለሮይተርስ የዜና ወኪል ገልጸዋል።

ቴህራን በረቂቅ የመግባቢያ ሰነዱ ላይ ባስቀመጠችው ስምምነት ማንኛውንም ዓይነት የኑክሌር መሣሪያ ከማምረት እና ከማግኘት ሙሉ በሙሉ ትቆጠባለች።።

ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ ከፍተኛ የኢራን ባለሥልጣን ይኸው ከአሜሪካ ጋር የተደረገው የረቂቅ ስምምነት ሂደት መቋጫ ማግኘቱን ለሮይተርስ አረጋግጠዋል።

#አሚኮ_ዜና #አሜሪካ_ኢራን_ስምምነት

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ክልሉ በርካታ ስፖርታዊ ውድድሮችን የማዘጋጀት አቅም አለው” አቶ መልካሙ ጸጋዬ