
ባሕር ዳር: ሚያዚያ 10/2018 (አሚኮ) የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ መሐመድ ባገር ጋሊባፍ አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው ወታደራዊ የባሕር ላይ እገዳ ካልተነሳ የሆርሙዝ ሰርጥ ክፍት ኾኖ አይቀጥልም ብለዋል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን አሜሪካ ወደምትፈልገው ድርድር እንድትገባ ጫና ለመፍጠር በኢራን ወጭ እና ገቢ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ እገዳ መጣሏ ይታወሳል።
በትናንትናው ዕለት የሆርሙዝ ሰርጥ ክፍት ከተደረገ በኃላ ዶላንድ ትራምፕ ባስተላለፉት መልዕክት የሰላም ስምምነት እስኪፈጠር ድረስ እገዳው እንደሚቀጥል አስታውቀው ነበር።
ይህንን ተከትሎ አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው ወታደራዊ የባሕር ላይ እገዳ ካልተነሳ የሆርሙዝ ሰርጥ ክፍት ኾኖ እንደማይቀጥል ኢራን በባለ ሥልጣኗ በኩል አስታውቃለች።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
