📈 3 ሺህ የኢንቨስትመንት ፈቃዶች በአማራ ክልል

5

 

ጎንደር፡ ሚያዝያ 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ” ኢትዮዽያ ታምርት እኛም እንሸምት” በሚል መሪ መልዕክት የማጠቃለያ መርሐ ግብር አካሂዷል። ማጠቃለያው በፓናል ውይይት፣ በባዛር እና ኤግዚቪሽን ነው የተካሄደው።

በመድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ተፈሪ ታረቀኝ
“የኢትዮዽያ ታምርት እኛም እንሸምት “ንቅናቄ ለባለፉት አራት ዓመታት በኢትትዮዽያ በርካታ ችግሮችን እንደፈታ አስረድተዋል።

ለዚህም ማሳያ የሚኾን በዘጠኝ ወር 2ሺህ 925 ባለሀብቶች በክልሉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንደወሰዱ አስረድተዋል። የአምራች ኢንዱስትሪው ከፍ ሲል የግብርና ምርትም አብሮ ከፍ ማለት አለበት ያሉት ምክትል ኀላፊው የሀገሪቱን የምርት ዘርፍ ከፍ ለማድረግ የኢትዮዽያ ታምርት ኢንሸቲቭ አስፈላጊ ዘርፍ ነው ብለዋል።

ባለፉት 9 ወራት በክልሉ ፦
🏭 137 አነስተኛ እና መካከለኛ ፋብሪካዎችን ምርት ማስጀመር እንደተቻለም ተናግረዋል።

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኜው ዘርፉ የሚታይ ለውጥ እየተመዘገበበት እንደሚገኝ አሳውቀዋል። የኢትዮዽያ ታምርት ንቅናቄ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መኾኑንም አመላክተዋል።

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ ግርማይ ልጃለም እንደገለጹት፦
📈 ከ2013 ዓ.ም እስከ 2017 ዓ.ም ባለው ግዜ ውስጥ 1ሺህ 457 ባለሀብቶች ፈቃድ ወስደዋል

🎯 241 የሚኾኑ ባለሀብቶች ወደ ሥራ ገብተዋል

ከእነዚህም መካከል 🏭 41 በኢንዱስትሪ ዘርፍ እና 200 የሚደርሱ በኢንቨስትመንት ሥራ መጀመራቸውን አስረድተዋል።

በዚህ ዓመት በሀገር ውስጥ የተመረተን ምርት ወደ ውጭ በመላክ 💰 143 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኜት እንደተቻለ እና 149 ሚሊዮን ዶላር ሊወጣ የነበረ ወጭን በሀገር በቀል ምርት መሸፈን እንደተቻለ አስረድተዋል።

በአሁኑ ወቅት በጎንደር ከተማ በማምረት ላይ የሚገኙ ⚙️ 169 ፋብሪካዎች ⚙️ ከ60 በመቶ በላይ የማምረት አቅም ላይ እንደደረሱም አቶ ግርማይ አስረድተዋል።

በዚህ ዓመት ሁለት አቁመው የነበሩ ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት መመለሳቸውን የጠቆሙት አቶ ግርማይ 11 አዲስ ኢንዱስትሪዎችም በዚህ ዓመት ወደምርት እንደገቡ አስረድተዋል።

በዘርፉ ለመሰማራት ፍቃድ አውጥተው ወደ ሥራ ያልገቡ 🚫 36 ባለሀብቶችንም ፍቃዳቸው እንደተሰረዘ ተናግረዋል።
በዘርፉ ያሉ ፈተናዎች፦
✍️የንግድ ፈቃድ ወስዶ ወደ ሥራ አለመግባት፣
✍️ፈቃድ በወሰዱበት ልክ ምርት አለመጀመር እና
✍️በተሰጣቸው ጊዜ ሠርቶ አለማጠናቀቅ

በመርሐ ግብሩ የተገኙ አልሚዎች በበኩላቸው የ”ኢትዮዽያ ታምርት እኛም እንሸምት” መርሐ ግብር ምርታቸውን ለማኅበረሰቡ እንዲያስተዋውቁ እና ሸማቹ በቀጥታ ከአምራቹ ጋር እንዲገናኝ ዕድል የፈጠረ መኾኑን አሳውቀዋል።

ዘጋቢ፦ ተስፋየ ጋሹ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ዛሬ የምንገነባው ለነገው ትውልድ ኩራት እና የብልጽግና ዋስትና ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነáˆ