
አዲስ አበባ: ግንቦት 09/2018 (አሚኮ)የዓለም የሙዚየም ቀንን በማስመልከት የተለያዩ የቅርስ ባለሙያዎች በአዲስ አበባ የሚገኙ ሙዚየሞችን ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ የቅርስ ባለሥልጣን ሠራተኞች እና ባለሙያዎች፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሠራተኞች እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት የቅርስ ባለሙያዎች የእዮቤልዩ ቤተመንግሥት፣ የኢትዮጵያ ሠራዊት እና የአንድነት ፓርክ ሙዚየሞችን ጎብኝተዋል።
የጉብኝት መርሐ ግብሩ የተዘጋጀው ሙዚየሞችን ለባሕል ልውውጥ፣ በሕዝቦች እና ባለሙያዎች መካከል የጋራ መግባባት እንዲኖር ለማስቻል ነው ተብሏል።
የጉብኝቱ አዘጋጅ የዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር ምንይል ታየ ኢትዮጵያ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ለሙዚየም ልማት ትኩረት ሰጥታለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ ሳይገለጡ የቆዩ ቅርሶቿን በሙዚየሞቿ በኩል እያሣየች እና በይበልጥ ወደ ማስተዋወቅ ተሸጋግራለችም ነው ያሉት።
ዘጋቢ: አንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
#የዓለምየሙዚየምቀን #የአድዋድልመታሰቢያ #የኢትዮጵያቅርሶች #InternationalMuseumDay #EthiopianMuseums #AdwaMemorialMuseum
