
ባሕር ዳር፡ ሚያዚያ 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን ታች ጋይንት ፣ ንፋስ መውጫ፣ ሰዲ ሙጃ እና ስማዳ ወረዳዎች ተሰማርቶ ሕግ እያስከበረ የሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አንድ ሬጅመንት በጽንፈኛው ቡድን 21 ታጣቂዎች ላይ የማያዳግም ርምጃ መውሰዱን አስቴውቋል።
የሀገር ጠላቶችን ተልዕኮ በመቀበል የሚንቀሳቀሰው ጽንፈኛ ቡድን ሀገራዊ ምርጫውን ለማስተጓጎል ሙከራ በሚያደርግበት ጊዜ ነው ርምጃ የተወሰደበት። ከደብረ ታቦር ወደ ንፋስ መውጫ የሚጓዘውን የምርጫ ቁሳቁስ ለማውደም አለኝ ያለውን ኃይሉን አሰባስቦ ቢመጣም በሠራዊቱ ብርቱ ክንድ እርምጃ ተወስዶበታል ሲሉ በቀጣናው የተሰማራው የሬጅመን አዛዥ ሻምበል ደርጎ ረደዒ ተናግረዋል።
በተካሄደው ኦፕሬሽን ሠራዊቱ በጽንፈኞች ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስዷል፤ ማርኳልም። 5 ክላሽ፣ 7 የቃታ ማሳሪያ፣ 1 ሽጉጥ፣ 7 ሞተር ሳይክል እና 50 ኩንታል እህል በመማረክ የተለያዩ አልባሳትን በቁጥጥር ስር ማዋሉም ተገልጿል ።
ከተደመሰሱት የጽንፈኞች አመራሮች መካከል አልዬ ደሳለኝ ዋና መረጃ ፣ ማረግ ቸሩ የቀጠናው ሎጅስቲክስ፣ መልካሙ ቢሆን ፋይናንስ እንዲሁም አበበ እምቢበል የጎብጎብ ሻምበል መሪ ይገኙበታል።
ሠራዊቱ ከአካባቢው የፀጥታ ኃይል እና ከኅብረተሰቡ ጋር በመሆን የሀገር ጠላቶችን አጀንዳ ለማስፈጸም የሚውተረተሩ ጸንፈኞችን እየተከታተለ መደምሰሱን እንደሚቀጥል ነው የተገለጸው። መረጃው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
