
በሀረር ከተማ የተካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከተማዋ ይበልጥ የቱሪስት መዳረሻነቷን እንድታልቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው የሀረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
በዛሬው እለት በሀረር ከተማ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር ተካሂዳል።
የሀረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሔኖክ ሙሉነህ ውድድሩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በርካቶችን ያሳተፈው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በስኬት ተጠናቋል።
ሩጫው ከስፖርታዊ እንቅስቃሴነቱ ባለፈ የሕዝቦችን አንድነት፣ ፍቅር እና የባሕል ትስስር የሚያጠናክር ታላቅ ሁነት መሆኑን ገልጸዋል።
ይህም በተለይ ከተማዋ የቱሪስት መዳረሻነቷን እንድታልቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አመላክተዋል።
በዚህም የከተማዋን ቅርስና ውበት ለዓለም በማስተዋወቅ የቱሪስት መዳረሻነቷን እንደሚያጎለብት ነው የተናገሩት።
እንዲሁም ለማኅበራዊ መስተጋብር እና አብሮነት መጎልበት ጉልህ ፋይዳ ያለው ይህ ኩነት በድምቀት እንዲካሂድና በስኬት እንዲጠናቀቅ ተወዳዳሪዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች ያበረከቱት አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
