የኢትዮጵያ አሸናፊነት እና የዘመኑ የሉዓላዊነት ምዕራፍ

12

የዘመኑ ትውልድ የአሸናፊነት ምስጢር የሚገለጸው በታሪካዊ አውድ ውስጥ ተዘፍቆ በመቅረት ሳይኾን ተግዳሮቶችን ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ታሪክን በአዲስ መልክ የመቅረጽ አቅምን በማጎልበት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የዘመኑ ትውልድ ያለፉትን ታሪካዊ ክፍተቶች በማረም በሰላም እና በጋራ ልማት ላይ እንዲተጋ፣ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ብቁ ኾኖ በራሱ ፈጠራ እና አቅም እንዲተማመን፣ በጠንካራ የሥራ ባሕል ሀገሩን እንዲገነባ በተለያዩ መድረኮች በተደጋጋሚ ተናግረዋል።

ይህም ትውልዱ በጠንካራ ሥነ ልቦና እና አቅም ላይ በመመሥረት የሉዓላዊነት እና የእኩልነት ተምሳሌት እንዲኾን አስችሎታል።

የድል መንፈሱን እውን ካደረጉ ዋና ዋና ማሳያዎች መካከል የውጭ ኀይሎችን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች በጽናት መመከት ዋነኛው ነው።

ሕዝብ ከሀብቱ አዋጥቶ እና በባለቤትነት ስሜት ተባብሮ ታላቁን የሕዳሴ ግድብ ከግብ ማድረሱ የውስጥ አቅምን በመጠቀም ራስን የመቻል ሥነ-ልቦና ማደጉን በግልጽ ያሳያል።

የዘመኑ ትውልድ በዲጂታል ዲፕሎማሲ እና በማኀበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት ሀገራዊ እውነቱን ለዓለም በማስተጋባት የውሸት ትርክቶችን የመበተን አቅም አሳይቷል።

የውጭን ትርክት በመስበር የራሱን እውነት የማድረስ ይህ ጥረት የሽንፈትን እና የተመጽዋችነትን አስተሳሰብ ሰብሮ ለመውጣት አስችሏል።

ሁለንተናዊው የለውጥ ጉዞ በግብርና እና በስንዴ ልማት መስክ ከምግብ ጥገኝነት የመውጣት ጅምሮችን እውን አድርጓል። ይህም ሀገሪቱ ከአስመጭነት ወደ ላኪነት እንድትሸጋገር እያደረጋት መጥቷል።

የሉዓላዊነት ማረጋገጫ ምሰሶዎች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በስታርት-አፕ ፈጠራዎች እየተደገፉ ቀጥለዋል። ወጣቶች የፈጠራ ባለቤቶች በመኾን ሀገራዊ ኢኮኖሚውን የማንቀሳቀስ አቅም ማሳየታቸው የትውልዱን ድል ይበልጥ ያጠናክረዋል።

ዛሬ ላይ ትውልዱ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ አልፎ የድል ባለቤት መኾኑ በቁስ ሳይኾን በሀገር ፍቅር እና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ሁለንተናዊ የድል ማረጋገጫ ታሪክ ነው።

በአሁኑ ወቅት ደግሞ ኢትዮጵያን ከቀሪው ዓለም ጋር በባሕር ለማገናኘት በሕዳሴ ግድብ እና በሌሎችም የልማት ሥራዎች ያሳየውን ጠንካራ እንቅስቃሴ በባሕር በር መሻቷም ለመድገም ቆርጦ ተነስቷል።

ለዚህም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የነበራትን ታላቅነት ለመመለስ ትውልዱ የችግሩን ልክ ተረድቶ የመሻገሪያ መርከቡን እየገነባ ነው ያሉት።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#Ameco #Generation_Excellence #NewEraofEthiopia

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_07_2019_ዓ_ም

✍️ በስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን ከዋሊያዎቹ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ባሕር ዳር ገባ!
Next articleብርድ እና ሐሩር የማይበግረው፣ ዳገት ቁልቁለት የማይገድበው የሉዓላዊነታችን ጋሻ!