‎የሻዕቢያ የውክልና የጥፋት ቀመር እና የኢትዮጵያ ዘመናዊ ምላሽ!

8

‎የሻዕቢያ መንግሥት ካይሮ ላይ ተጸንሶ፣ ካይሮ ላይ ተወልዷል። የካይሮ መንግሥትን ተልዕኮ በመቀበል እና በመፈጸም ኢትዮጵያን ለማዳከም ዘወትር ይደክማል። በኢትዮጵያ ውስጣዊ ግጭቶች እንዲበራከቱ ታጣቂዎችን በገንዘብ፣ በሎጂስቲክ እና በመሣሪያ ድጋፍ ያደርጋል።

‎‎ሻዕቢያ የኤርትራ ሕዝብን አጥሮ ከሥልጣኔ፣ ከዲጂታል ሥርዓት፣ ከኢኮኖሚ ዕድገት እንዲርቅ አድርጎ ቆይቷል። አብሮ መሥራት፣ በኅብረት ማደግ፣ ለቀጣናው ኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን ድርሻ መወጣት የሻዕቢያ መንግሥትን አይታየውም።

‎‎ይልቁንስ የግብጽ እና የሌሎች ሀገራትን ተልዕኮ መቀበል፣ መፈጸም፣ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናን ማፍረስ፣ የሽብርተኞች መዳረሻ መኾን መገለጫዎቹ ናቸው። በዚህ የተነሳ የኤርትራ ሕዝብን ኢኮኖሚ ገድሏል፣ ነጻነትን ቀብሯል፣ ኢንቨስትመንቱን አድቅቋል፣ ሕዝቡን ለስደት ዳርጓል።

‎‎የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የፓለቲካ ሳይንስ ምሁር ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ ኢትዮጵያ ብዙ ጠላቶች የሚመኟት ታሪካዊ ሀገር ናት ብለዋል። ግብጽ ዓባይን ለመቆጣጠር ለዘመናት ብትሞክርም እንዳልተሳካላት ተናግረዋል።

‎‎የሻዕቢያ መንግሥት ሥልጣንን በብቸኝነት በመቆጣጠር፣ የሕዝብን መብት በመጨቆን፣ ተጠያቂነትን በማጥፋት፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን ባለማድረግ ሕዝቡን ከዓለም ማራቁንም ተናግረዋል።

‎‎እንደ ፕሮፌሰሩ ገለጻ በጀት፣ ፍትሕ፣ ዴሞክራሲ፣ መሠረተ ልማት በሻዕቢያ መንግሥት አይታወቅም። ሻዕቢያ በኢትዮጵያ እና በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ለታጣቂዎች የሎጂስቲክ፣ የገንዘብ እና የጦር መሣሪያ ድጋፍ በማድረግ ግጭትን በማስፋት ሀገርን ለማዳከም ይሠራል ነው ያሉት።

‎‎የሻዕቢያ መንግሥት የኤርትራ ሕዝብን ኢኮኖሚ ዘግቷል፣ ሕዝቡ የለውጥ ጎዳና ላይ እንዳይራመድ አድርጓል ብለዋል። ኤርትራን ማሳደግ ሳይኾን ማደም እና ማሳደም የሻዕቢያ መንግሥት መንገድ መኾኑንም ተናግረዋል። በሱዳን፣ በአንጎላ፣ በኡጋንዳ፣ በቻድ እና በሌሎች ሀገራት ጣልቃ በመግባት ግጭትን ለመፍጠር መሥራቱንም ገልጸዋል።

‎‎ወጣቱ የሥራ ዕድል ሳይኾን የመሣሪያ አማራጭ ብቻ እንደሚቀርብለትም ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ በመግባት የሀገርን ሉዓላዊነት ለማጥፋት ሠርቷልም ብለዋል።

‎‎ኢትዮጵያ ፈተናዎችን በማለፍ፣ የኢኮኖሚ ዕድገቷን በማረጋገጥ፣ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን በማስፋት፣ ቴክኖሎጂን በስፋት በመጠቀም የለውጥ ጎዳና ላይ መኾኗን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በግብጽ እና በሻዕቢያ የደረሰባትን ታሪካዊ በደሎች በትዕግሥት አልፋለች፤ አሁን ግን ኢትዮጵያ ዝም አትልም ክብሯን ታስጠብቃለች ነው ያሉት።

‎‎ኢትዮጵያ በጋራ ተጠቃሚነት፣ በሰጥቶ መቀበል መርሕ፣ በሰላማዊ አማራጭ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ለመሥራት ሁሌም ዝግጁ ናት ብለዋል። ኢትዮጵያ ዘመናዊ የጦር ቴክኖሎጂዎችን፣ ድሮኖችን፣ ተወንጫፊ ጀቶችን፣ የጦር አውሮፕላኖችን በመታጠቅ የቀጣናውን ሰላም ለማጽናት እየሠራች መኾኑንም ተናግረዋል።

‎‎በኢ-ተገማች የምሥራቅ አፍሪካ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር እየሠራች መኾኑንም ገልጸዋል።

‎‎#የመደመር_መንግሥት!

‎‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

‎‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_07_2019_ዓ_ም

‎‎✍️ ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

 

Previous article‎በኮሪደር ልማት የኢትዮጵያ ከተሞች እየፈኩ ነው!
Next articleየሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን ከዋሊያዎቹ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ባሕር ዳር ገባ!