“በአነስተኛ ካፒታል የተጀመሩ ኢንቨስትመንቶች በጥቂት ዓመታት ውስጥ የካፒታል አቅማቸውን ማሳደግ ተችሏል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

9
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በሐረር ከተማ በግብርና ኢንቨስትመንት የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ወደ አዲስ ምዕራፍ እየተሸጋገሩ ነው ብለዋል።
በአነስተኛ መነሻ ካፒታል የተጀመሩ ኢንቨስትመንቶች በጥቂት ዓመታት ውስጥ የካፒታል አቅማቸውን ማሳደግ ተችሏል ነው ያሉት። የድለባ ጊዜያቸውን የጨረሱ የሐረር ሠንጋዎችን፣ በየሦሥት ወሩ ለውጭ ገበያ በማቅረብም የውጭ ምንዛሬ ግኝት እንዲጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ።
በቀጣይም በዚህ ዘርፍ በሰፊው በመሰማራት የሀገራችንን ኢኮኖሚ እና የውጭ ምንዛሬን ለማሳደግ በሚደረገው ሂደት ውስጥ በየደረጃው ያሉ መሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለደርሻ አካላት በትጋት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየአማራ ክልል የዓሣ ምርት አዲስ ተስፋ!
Next articleከዝቅተኛ አምራችነት ወደ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት- የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ጉዞ!