
ኢትዮጵያ አሰብ፣ አዱሊስ፣ ገምበዛ፣ ዘይላ እና ምጽዋ የተሰኙ የቀይ ባሕር ወደቦች እንደነበሯት የታሪክ መረጃዎች ያሳያሉ። በታሪክ በተፈጠሩ እጥፋቶች እና በፖለቲካ ሴራ ግን ከቀይ ባሕር ቀጣና ርቃ ቆይታለች። ከባሕር በር መገለሏ ደግሞ በየዓመቱ ረብጣ ገንዘብ ለወደብ ኪራይ እንድትከፍል አድርጓታል።
ከወደብ መገለሏ የባሕር ኀይሏን አፍርሷል። በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፣ በሀገሪቱ የዕድገት ግስጋሴ ላይ ማነቆም ፈጥሮ ቆይቷል።
ያዕቆብ ኀይለማርያም (ዶ.ር) “አሰብ የማን ናት” በሚለው መጽሐፋቸው በወቅቱ ሀገሪቱን ያሥተዳድር የነበረው ሥርዓት”ወደብ ለዕድገት አስፈላጊ አይደለም፣ ወደብ ማጣት አይጎዳንም” በማለት በፖለቲካዊ ሤራ ኢትዮጵያ ከባሕር በር እንድትገለል ማድረጋቸውን አትተዋል።
በወቅቱ የነበረው ሥርዓት” አሰብን ወደ ኢትዮጵያ እንመልስ ማለት ከኢትዮጵያ መንግሥት እምነት እና መርሕ ውጭ ነው” በማለት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል መፈጸሙ በመጽሐፉ ተጠቅሷል።
በታሪክ ኢትዮጵያን ለማዳከም የመጡ ታሪካዊ ጠላቶች ቀይ ባሕርን በመጠቀም ጥቃት ይፈጽሙ እንደነበር በመጽሐፉ ተቀምጧል።
የሽብርተኞችን እና የጠላትን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ያግዛል። የወጭ እና የገቢ ንግድ እንቅስቃሴን ያሳልጣል፣ በየዓመቱ ለወደብ ኪራይ የሚወጣን ወጭ በማስቀረት መሠረተ ልማት ላይ እንዲውል ያስችላል፣ የማኅበረሰቡ ኑሮ እንዲሻሻልም ያደርጋል።
የባሕር በር ተጋሪነታችን የተለወጠው፣ የተጽዕኖ አድማሳችን ሲኮሰምን የኖረው ፈልገን ብቻ አይደለም፤ ተገደን ጭምር ነው ብለዋል። አቅም በነበረን ወቅት የራሳችንን ጉዳይ ራሳችን ወስነናል፣ በተዳከምን ጊዜ ግን ሌሎች በእኛ ላይ ወስነውብናል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያለ ባሕር በር እውን ሊኾን አይችልምና በሰጥቶ መቀበል መርሕ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ተግተን እንሠራለን ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
