
ባሕር ዳር: ጥቅምት 16/2019 ዓ.ም (አሚኮ) #የግድቡ ርዝመት 890 ሜትር ነው፤
#የግድቡ አጠቃላይ ቁመት 114 ሜትር ሲሆን፣ 77 ሜትሩ ከመሬት በላይ እንዲኹም 37 ሜትሩ ከመሬት በታች የተገነባ ነው።
#ግድቡ 9 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የአፈር እና የድንጋይ ሙሌት አለው።
#የውኃ ማከማቻው 870 ሄክታር መሬት ይሸፍናል።
#አጠቃላይ 185 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ የመያዝ አቅም አለው።
#ከሚይዘው ውኃ ውስጥ 116 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትሩ ለግብርና መስኖ ልማት ይውላል።
#በመስኖ የሚለማው የመሬት ስፋት ከ17 ሺህ ሄክታር በላይ ነው።
#32 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ ለጎንደር ከተማ እና ለአካባቢው ከተሞች የመጠጥ ውኃ አገልግሎት ይመደባል።
#ፕሮጀክቱ ለጎንደር ከተማ ቅርብ በመኾኑ የከተማ ግብርና እና የአሳ እርባታን ይውላል፤ የቱሪዝም እንቅስቃሴን ለማስፋፋት ምቹ ኹኔታ ይፈጥራል።
የመረጃ ምንጭ፦ የመገጭ መስኖ ልማት ፕሮጀክት
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
